News

በሆቴልና ቱርዝም ዘርፍ የዘንድሮው የመሳላ አዋርድ ተሸላሚ

የታታሪነት መገለጫ እና የፅናት ተምሳሌት በሆነው፤ መቻልን ከቃል በላይ በተግባር ባሳየው፤ ለበርካታ ወጣቶች የስኬትን መንገድ ባመላከተው፤ 'ይቻላል!' በሚለው የተግባር መርህ በብዙዎች ዘንድ በስፋት በሚታወቀው በወጣቱ ባለሀብት አብርሃም ገሙ በሺንሽቾ ከተማ የተገነባ ውብ ሆቴል ነው የይቻላል ሆቴል።

በከምባታ ዞን በሆቴል ቱሪዝም ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶችን የቀረፈ ለውጪም ሆነ ለሀገር ውስጥ ቱርስቶች የተሟላ የምግብ የመጥ የመኝታ የመዝናኛና ሌልችንም አገልግሎቶች በተሟላ ሁኔታ መስጠት የሚችል በለ ሶስት ኮከብ ሆቴል ነው ይቻላል ሆቴል።

በዞኑ እያደገ የመጣውን የየቱሪዝም መነቃቃት ያገዘ እና ለዘርፉ ትልቅ አበርክቶ እየሰጠ የሚገኝ ሆቴል ነው። ተመርቆ ለአገልግሎት ከበቃ ጊዜ ጀምሮ በርካታ የሀገር እና የውጪ ሀገር ዜጎችን ተቀብሎ በዘመነ መስተንግዶ በማስተናገድ ወደዞኑ የሚመጡ ቱሪስቶችን በልዩ እንክብካቤ በመቀበል በሆቴል ቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።

የይቻላል ሆቴል በእነዚህ እና ከላይ በተጠቀሱ በርካታ መልካም ተግባራት በሆቴል ቱሪዝም ዘርፍ የዘንድሮው የመሳላ አዋርድ ተሸላሚ ሆኗል። እንኳን ደስ አላችሁ!

በሳይንስ ዘርፍ የመሳላ አዋርድ አሸናፊ የሆኑት ኢንጂነር እና ሳይንቲስት ጌታሁን ሄራሞ

ሳይንቲስት ኢንጂነር Getahun Heramo ተመራማሪ፣ ደራሲ፣ የፈጠራ ባለቤት፣ ምሁር ባለ ሐብትና ኬሚካል ኢንጅነር ናቸው። ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ ለአንድ መቶ ዓመታት ያህል ሀገራችን ከውጭ ሀገር ስታስገባ የነበረውን የሕትመትና የሠዓሊ ቀለሞችን ቀመር በብቸኝነት በሀገር ውስጥ በመቀመር ኢትዮጵያ ውስጥእንዲመረት ያደረጉና ለነዚሁ ምርቶች የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ያስቀሩ የቀለም ፎርሙሌሽን የፈጠራ ስራ ባለቤት ናቸው።

በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተለይም የሕትመትና የሠዓሊ ቀለማት የሚያመርቱ እጅግ በጣም ጥቂት ኩባንያዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ሆኖም ሁሉም በሚባል ደረጃ በውጭ ሀገር በተለይም በአውሮፓና በሕንድ ባለሙያዎች የተቀመሩ ናቸው፤ ስለዚህም አሁን ባለው መረጃ በምሥራቅ አፍሪካም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ደረጃ አኳያ ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ ብቸኛው ሀገር-በቀል የሕትመትና የሠዓሊ ቀለሞች ኢትዮጵያዊ ፎርሙለተርና አምራች መሆናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል።

ከመደበኛ ሙያቸው ባሻገር ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች ሀሳብን በሀሳብ በመሞገት ይታወቃሉ። የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸውን በመጠቀምም የአዲስአበባ ከተማ ታሪካዊ ሕንፃዎች የቀለም ዕድሳትና የከተማው የቀለም ዲዛይን ሙያውን በተከተለ መንገድ እንዲከወን በመሞገት በከተማው ከንቲባ ፅ/ቤት ተቀባይነትን ያገኘ ውጤታማ ሥራ ሰርተዋል። ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ የከምባታ እናት ፍሬ የሆነ ኩሩ ኢትዮጵያዊም ናቸው። ሳይንቲስት ጌታሁን ሄራሞ በሳይንሱ ዘርፍ ባደረጉት የፈጠራ ሥራ ቀደም ሲልም የተለያዩ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ሽልማቶችን ተጎናፅፈዋል።

1. ከኢትዮጵያ ኬሚካል መሐንዲሶች ማሕበር "Industrial Innovation Award" በሚል ሽልማት አግኝተዋል። 2. ከዓለም ባንክ (World Bank) Best Business Idea Award for the Successful Import Substitution በሚል ከፍተኛና አለም አቀፋዊ ሽልማት ተጎናፅፈዋል።

ባለ ምጡቅ አእምሮ ሳይንቲስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ካሏትና ማህፀን ለምላሟ የከምባታ እናት አምጣ ከወለደቻቸው ምርጥ የሀገር ውስጥ ምሁሮች አንዱና ዋነኛው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥም የቀለም ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ሥነ ልቦናዊ ተፅዕኖዎች ዘመናዊ በሆነ መልኩ እንዲጠኑ መሠረት የጣሉ የኬሚካል መሐንዲስም ናቸው። ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ የጠቅላይ ሚኒስትር የዶ/ር አብይ አህመድ ቢሮን ጨምሮ ለሚኒስትሮችና ለከፍተኛ ባለስልጣናት በተለያዩ ጊዜዎች ከሙያቸው ጋር በተገናኘ በቢሮ አደረጃጀትና የቀለም ሥነ ልቦናዊ ተፅዕኖዎች ዙሪያ ሥልጠናዎች ሰጥተዋል።

በጤና እና በህይወት ዘመን አገልግሎት ዘርፍ የመሳላ አዋርድ ያሸነፉት ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ

ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ እና ያስሸለሟቸው ዋና ዋና አገልግሎቶቻቸው፦ -25 ዓመት(ከ1998ዓ.ም ጀምሮ)የሕክምና፣የምርምር፣ ሀኪሞችን የማስተማርና የመምራት አገልግሎት

-በነዚህ አመታት ሀገራችን ባለፈችባቸው በሁሉም ጦርነቶችና ግጭቶች የጉዳት ሰለባ የሆኑትን በኦፕራሲዮን በማከም፣በየግንባሩ በመዝመት፣በማስተባበር፣ውድ የአጥንት ሕክምና ዕቃዎችን ባላቸው ስምና መልካም ግንኙነት ውጭ ሀገር ካሉ ወዳጆቻቸውና ኩባንያዎች በነፃ ወደሀገራችን የተለያዮ ሆስፒታሎች አስመጥቶ በነፃ ማከፋፈል (የዱራሜ ሆስፒታልን ጨምሮ 15 የአጥንት ህክምና ማዕከላት አቋቁመዋል)

-በሀገሪቱ ትልቁንና ብቸኛውን የአጥንት የሰብ-እስፔሻሊስትና የስፔሻሊስቶች ማሰልጠኛ ተቋም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚገኘውን በከፍተኛ ውጤታማነት ከበርካታ አመታት ጀምሮ አሁንም መምራት -ከ20 ሺህ በላይ ከባባድ በኦፕራሲዮኖች ማድረግ

-ከ250 በላይ የአጥንት ቀዶ ሕክምና እስፔሻሊስት ሐኪሞችን በአመራር ዘመናቸው አሰልጥነው አስመርቀው ዕቃ አስታጥቀው ወደ መላ የሀገራችን ክፍሎች በማሰማራት በተለይ በነዚህ የግጭትና የጦርነት ዓመታት በከፍተኛ ብቃት እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ሀላፊነታቸውን መወጣት ላይ ይገኛሉ። ፕሮፌሰር እጁን ይዞ ያላስተማረው እውቅ የአጥንት ሐኪም የለም።

-በነፃ ማገልገል ምርጫቸው ሲሆን ለዚህም ማሳያና ምሳሌ ለመሆን ከፓርላማ የሕዝብ ውክልና ምንም ደሞዝ/ክፍያ አይቀበሉም፣መኪና ነዳጅ ጥቅማጥቅም አይቀበሉም፣ከየትም ምንም አበል አይቀበሉም አይወዱም(የደሀ በጀት በዓበል አይነካ ይላሉ)፣ቤትና መሬት ስጦታ ምናምን አይቀበሉም።ጤናና ብቃት ፈጣሪ ሠጥቶኛል ሠርቼ ማግኘት ብሎም ማካፈል እችላለሁ ብለው በዞናችን ወይም ስለጥሩ ጉዳይ የትም ቦታ መዋጮ ካለ ያዋጣሉ። ሁሉም ሳይሆን ፌስቡክ ላይ የሚለጠፈውን በአመት ለተለያየ ያዋጡትን ብንደምር አሀዙን ማየት ይቻላል።